المدة الزمنية 10:14

ኤርቱግሩል | Ertugrul | Ertugrul film Amharic | የሞንጎሎች አስገራሚ ታሪክ ክፍል 2

بواسطة ARIF MEDIA
5 108 مشاهدة
0
95
تم نشره في 2021/02/27

#ሞንንጎሎች_በጂንጊስ_ኻን_ዘመን የአለማችን ሀያሎቹ ወራሪዎች ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ( Seid social - ሰኢድ ሶሻል ) ክፍል -2 ክብሯን አንባቢዎቼ በክፍል አንድ የሞንጎሎች ታሪክ የሞንጎሎችን አነሳስ ከነብዩ ኑህ ልጅ ከያፌት እስከ ጂንጊስ ኻን ያለውን ታሪክ አይተናል ። ቱርኮች ሞንጎሎች ቻይናዎችና ሩሲያዎች ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸው የያፌት ትውልዶች መሆናቸውንም ተመልክተናል ። በተለይም ደግሞ በቱርኮችና በሞንጎሎች መካከል ያለው የቤተሰብነት ትስስር ከፍተኛ መሆኑንና ሞንጎሎች ለዘመናት በቱርኮች አገዛዝ ስር እንዳሳለፉ ተመልክተናል። ዛሬ ከታሙጂን ( ጀንጊስ ኻን ) ጀምሮ ያለውን ታሪካቸውን እንመለከታለን። የታሙጂን አባት የሱገይ ይባላል ። አባቱ የጎሳው መሪና ተበታትኖው የሚኖሩት የምንጎል ጎሳዎች ኮንፌዴሬሽን ጦር መሪም ነበር ። እናም አባቱ የሱገይ ወደ ታታሮች ሄዶ በነበረበት ጊዜ መርዝ አብልተው ገደሉት ። ታታሮች የቱርክ ጉሳዎች ነበሩ። ያኔ ታሙጂን እድሜው 9 ብቻ ነበር ። በዘጠኝ አመቱ አባቱን የተነጠቀባት ቅፅበት የታሙጂንን ህይወት የቀየረች ቅፅበት ነበረች። " ከዚህ በሗላ ታሙጂን ልጅ አይደለም ጠላቶቹንም ሳይበቀል መቼም አይምሬቸውም" በማለት ለራሱ ቃል ገባ። የታሙጂን እናት ሆሉን ትባላለች ። አባቱ እናቱን ያገባው አስገድዶ በመጥለፍ ነበር ። አባቱን በግድያ ያጣው ታሙጂን ጎሳውን ጭምር የሚያስጠጋው ጠፋ ። የእናቱ ቤተሰቦችም አናውቃችሁም አሏቸው ። እናም ስደትን ህይወት አደረጉት ። እያደኑ ውለው እያደኑ ማደር ! ከአደን የሚገኝን ነገሮች ብቻ እየተጠቀሙ እንደ አውሬ መኖር የታሙጂን ጎሳዎች እጣፈንታ ሆነ ። በዚህ መካከል ነው በታሙጂንና በወንድሙ መካከል የጎሳው መሪነት ይገባኛል ፀብ የተነሳው ። የታሙጂን ታላቅ ወንድሙ ከእናቱ የሚወለድ አልነበረም ። እናም የታሙጂን ወንድም ቤግተር የአባቴ ስልጣን ይገባኛል አለ ። የአባቴ ሚስትም ከዚህ በሗላ ሚስቴ ናት በማለት አወጀ ። በዚህ ጊዜ ነው ታሙጂን ወንድሙን ቤግተርን የገደለው ። ታሙጂን እያልኳችሁ ያለሁት ጂንጊስ ኻንን እንደሆነ ልብ በሉ። ታሙጂን ወንድሙን ከገደለ በሗላ የጎሳውን መሪነት ተረከበ ። እናም አባቱ በዘጠኝ አመቱ ያጨለትን ሚስቱን አገባ ። የታሙጂን ጎሳዎች የራሳቸውን ድንኳን ቀልሰው መኖር ጀመሩ ። ግና በዚህ መሃል ሌላኛዎቹ የሞንጎል ጎሳዎች የታሙጂንን ጎሳ ወረሩ። ሁሉንም የጎሳው አባላት አባላት ገደሉ ። ሚስቱን ግን ማርከው ይዘዋት ሄዱ ። ታሙጂንም ጥቂት ወታደሮቹን ብቻ ይዞ አመለጠ ። በዚህ ወረራ ታሙጂን ውስጡ ተቃጠለ ። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሚስቱ ምርኮኛ ሆና የጠላት መጫዎቻ መሆኗ አንገበገበው ። እናም አጋር ፈልጎ ከደም ወንድሙ ጋር ሄደ ። የደም ወንድሙ ጃሙካ ታሙጂንን ተቀበለው አብረው ጥምረት ፈጥረውም ጎሳውን ያወደሙበትን ጎሳዎች ተበቀሏቸው ። ሚስቱንም አስመልጦ አመጣ ። የታሙጂንና የጃሙካ ጥምረት ግን ረጂም ጊዜ ሊዘልቅ አልቻለም ። ታሙጂን የጃሙካንን የደም ወንድምነት ለማረጋገጥ አሰበ ። እናም ለጃሙካን እንደዚህ አለው " ይህ የእኛም መሬት ነው ስለዚህ እዚሁ አብረን እንኖራለን " አለው ። በዚህ ጊዜ ጃሙካን ተቆጣ ። እኛና እናንተ ጠላት ጎሳዎች ነበርን ካስፈለገ አሁንም እንዋጋለን አለውና ተለያዩ ። ጃሙካን ጦሩን አደራጅቶ በደም ወንድሙ በታሙጂን ጎሳዎች ላይ ጥቃት ፈፅሞ እጅቅ ሰቅጣጭ ውድመት አደረሰ ። አብዛኛዎቹን ሰዎች በሰይፉና ከቤት ውስጥ በማቃጠል ፈጃቸው ። የተረፉትን በተፍለከለከ ዘይት ውስጥ ከተታቸው ። ይህ ታሙጂንን አስቆጣ ። እናም ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ጥምረት በመፍጠር በጃሙካን ላይ አፀፋ ወሰደ። ታሙጂን በቁጥር በጣም የሚበልጠውን የጃሙካንን ጦር በአስደናቂ የታክቲክ ልህቀት አፈራርሶ ደመሰሰው ። ጃሙካን አመለጠ ግና የገዛ ታማኝ ሁለት ወታደሮቹ ከድተው ለታሙጂን አመጡለት ። እነርሱ የታሙጂንን ጠላት አምጥተው ምህረትን ከታሙጂን ለማግኘት አስበው ነበረ። ግና አልተሳካላቸውም ። ታሙጂን በተፈጥሮ ከሃዲና ፈሪ ፈፅሞ አይወድም እነዚያ ጃሙካንን ያመጡ ወታደሮችን ግደሏቸው ብሎ ተገደሉ ። ጃሙካንን ግን ይቅር ብየሃለሁ አለው ። የደም ወንድሜ የድሮ ጓደኛየ እኔ ለአን የይቅርታ ልብ አለኝ አለው ። ግና ጃሙካን እምቢ አለ ። " በዚህ ሰማይ ላይ ያለው አንድ ፀሀይ ብቻ ነው ። ሁለት ፀሀይ ሊኖር አይችልም ስለዚህ እኔን እንድትገድለኝ እጠይቅሃለሁ ግና ስትገድለኝ የክብር አገዳደል ይሁንልኝ ደሜ እንዳይፈስ አድርገህ ግደለኝ " በማለት ታሙጂንን ተማፀነው ። ታሙጂንም የጃሙካን ጥያቄ በመቀበል ወገቡ ተቀጭቶ እንዲገደል አደረገው ። በቱርኮችና በሞንጎሎች ህግ የመሪ ቤተሰቦች ደማቸው አይፈስም ። ሲገደሉ ደማቸው እንዳይፈስ ተደርጎ ነው የሚገደሉት ። በማነቅ ወይንም ወገብ በመቅጨት ሊሆን ይችላል። ታሙጂን ጃሙካንን ከደመሰሰ በሗላ መላው የሞንጎል ጎሳዎች በዙሪያው ተሰባሰቡም ። ታሙጂን መሪያችን ነው በማለት በእርሱ ትእዛዝ ስር ገቡ ። ከዚያም እርሱን ለማንገስ ሁሉም የሞንጎል ጎሳ መሪዎች ተሰባሰቡ ። በዚያ የንግስትና ስነስርአት ላይ ታሙጂን የአለማቱ ንጉስ ተሰኘ - #ቺንጊስ_ኻን ! ቺንጊስ ማለት ተንጊስ ከሚለው የቱርክኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ውቅያኖስ ማለት ነው ። የጂንጊስ ኻን ሌላኛው ስሙ ሞንግኬ ተንግሪን ይሰኛል ። ሁለቱም የፍጥረተ አለሙ ንጉስ ( Universal king ) ማለት ነው ።ፈረንጆቹ ጄንጊስ ኻን ይሉታል ። ጂንጊስ ኻን የአለሙ ንጉስ ! ስለዚህ ከአሁን በሗላ ታሙጂን ማለታችንን ትተን ጄንጊስ ኻን እንላለን ማለት ነው ። ጄንጊስ ኻን ሞንጎሎች በታሪካቸው አይተውት የማያውቁትን አንድነት አይተውት የማያውቁትን ሀያልነት ያጎናፅፋቸው ጀመር ። ከአሁኑ ሳይቤሪያ ሩሲያ እና ከአሁኗ ሞንጎሊያ አጎራባች መንግስቱን አቋቋመ ። ሞንጎሎች በታሪክ አንድ መንግስት ሆኑ ። ጄንጊስ ኻን ሞንጎሎችን ካዋሀደ በሗላ የግዛት ማስፋፋት እቅዱ ከሞንጎሊያ ምድርም ሰፋ ። ድሮስ የአለሙ ንጉስ ለምን ተባለና! እናም የመጀመሪያ ወረራውን በቻይናው ዢን ዢያን ስርወመንግስት ላይ ፈፀመ ። ዢን ዢያን ጠንካራ የሚባል መንግስት አልነበረምና ንጉሱ እጅ ሰጥቶ በጄንጊስ ኻን ስር ተጠቃለለ። ቻይና በድንበር አካባቢ የሚነሱ መንግስታትን አትታገስም። ዢዮንኙ እና ኡይጉር የመሳሰሉ የቱርክ መንግስታት ለበርካታ ክፍለዘመናት ቻይናን አንበርክከው ከፍተኛ ግብር ሲያስከፍሏት ቆነጃጅት ሴቶቾን እየወሰዱ እቁባቶች ሲያደርጉባት ኖረዋል ። እና ጄንጊስ ኻን ተነሳ ሲባል ቻይና ጊዜ ማጥፋት አልፈለገችም ። ወዲያው ለእርምጃ ተዘጋጀች። የቻይናው #ጂን ስርወመንግስት አንድ ትልቅ ስህተትን ፈፀመ ። ጄንጊስ ኻን ግብር ለቻይና እንዲከፍልና በቻይና ስር እንዲተዳደር የሚጠይቅ ትእዛዝ ላከለት ። በዚህ " የአለሙ ንጉስ " ጂንጊስ ኻን ተቆጣ ። እኮ እንደት ብደፈር ነው ? አለ ። እናም ከ 50,000 በላይ ከሞንጎልና ቱርኮች የተውጣጣ ሰራዊቱን ይዞ ወደ ቻይና ተመመ ። ግና ቻይናዎች በመሳሪያ ቴክኖሎጅም በሎጀስቲክም ሆነ በተዋጊ ብዛት ይበልጡት ነበረ ። ጂንጊስ ኻን ወረራውን ጀመረ ቻይናዎችም በስኬት መከቱ ። በዚህ ጊዜ ጄንጊስ ኻን አፈገፈገ - የማታለል ማፈግፈግ ! አሳቻ ቦታና ጊዜ ጠብቆ የቻይናው ንጉስ ወደ ሌላ የከተማዋ ክፍል በተጓዘበት ቅፅበት ቤጅንግን አመድ አደረጋት ። ቤጂንግ ያን ጊዜ #ዦንግዱ ነበር ስሟ። ከአለም እጅግ የተራቀቀችው ከተማ ወደ አመድነትኤርቱግሩል በአማርኛ |ኤርቱግሩል |Ertugrul season 1 |ሞንጎሎች ከጀንጊስ ኻን በኋላ |ኤርቱግሩል አማርኛ,ኤርቱግሩል በአማርኛ,ኤርቱግሩል 1,ኤርቱግሩል ፊልም,Dirilis,ertugrul season 1,ertugrul season 2,ertugrul season 3,Ertugrul,ቃና,የአማርኛ ፊልም

الفئة

عرض المزيد

تعليقات - 4