المدة الزمنية 15:00

[አስደሳች ዜና ቦታው ተፈቀደ]የፓትርያርኩ ጉዳይ ቤተክርስቲያኖቹ ወድመዋል ጋዜጠኛው ሀቁን ተናገረ

122 132 مشاهدة
0
3.3 K
تم نشره في 2022/01/15

#gizetube #ግዜቲዩብ ሰላም ይኑረን ተስፋን አንጣ ውድ የግዜ ቲዩብ መርሀግብር ተከታታዮች ጥር 7 በዚህች ቀን ቅድስት ሥላሴ በኃጢያት የተገነባውን የሰናኦር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሶስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ቀን ነው፤ ሙሉ ታሪኩ ዘፍጥረት 11 ፤1 ላይ ይገኛል፤ እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ። ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው። እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ ይላል። ( “እግዝያብሔርም አለ” አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ኑ እንውረድ ሶስትነታቸውን፤) ሥላሴ በስም አአካል በግብር ሶስት ናቸው፤የስም ሶስትነታቸው እንደምን ነው ቢሉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፤ የግብር ሶስትነታቸውስ እንደምን ነው ቢሉ አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ፤የአካል ሶስትነታቸውስ እንዴት ነው ቢሉ ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመሆኑ የሥላሴ ገጽ አካል ፊት እንደ ሰው ነውን ቢሉ አዎን እንደ ሰው ነው ነገር ግን የሰው ውሱን ጠባብ ፈራሽና በስባሽ ነው የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም በሰማይና በምድር በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ህያው ባህርይ ነው ኢሳ 66 ፤ 1። የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት በፈቃድ በስልጣን በምክር ወዘተ በመሳሰሉት ነው ቅድስት_የሚል የሴት ቅጽል የተቀጸለላቸው ባሕርያቸው ታይቶ ነው፡፡ ✞ልጅ ከእናቱ ባሕርይ እንዲገኝ ይህም ዓለም ከሥላሴ ባሕርይ ተገኝቷልና፤ ✞እናት ለልጇ የሚያሻውን አስባ እንድታቀርብለት ሥላሴም ለፍጥረት ሁሉ የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድመው ያዘጋጁለታል ይሰጡታልም፡፡ ማቴ. ➏፥➌➋ ✞አንድም እናት ልጇ ቢያስቀይማት ፈጽማ እንዳትጣላው ሥላሴም ሠርቀው አመንዝረው ቢበድሏቸው ንስሓ ገብተው ቀኖና ይዘው ቢለምኗቸው ይቅር ይላሉና፡፡ “ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆን ሦስት ስለሚሆኑ ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡ ሥላሴ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለና የሚኖረውን አምላክ ለመግለጽ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቴዎፍሎስ በ169ዓ.ም ነው፡፡ኋላም በኒቅያ ጉባዔ 318ቱ ሊቃውንት አጽንተውታል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረውን የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ለእኛ በሚረዳ ቋንቋ ገለጡት እንጂ አዲስ ትምህርት አላመጡም፡፡ ይልቁንም ነገረ ሥላሴን ሳይረዱ በሥላሴ መካከል የክብርና የተቀድሞ ልዩነት ያለ አስመስለው በክህደት ትምህርት የተነሱ መናፍቃንን ክህደት ለማስረዳት፣ የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን የቀናች ሃይማኖት ለመግለጥ ምሥጢረ ሥላሴን አብራርተው አስተምረዋል፡ ምስጢረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም በእምነት የተገለጠ፣ ያለ እምነትም የማይመረመር ስለሆነ ነው፡፡ ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡ ስለዚህም በአንድ አምላክ፣ በሦስቱ አካላት እናምናለን፡፡ የክርስትና ዶግማ (መሠረተ እምነት) በምስጢረ ሥላሴ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ምስጢረ ሥላሴ የእምነታችን ዋነኛው ምሰሶ ነው፡፡ በመዳን ትምህርት ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው ምስጢረ ሥላሴ ነው፡፡ ለመዳናችንም መሠረት ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁላችን የተጠመቅነው በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ነው (ማቴ 28፡19)፡፡ የሥራችን ሁሉ መጀመሪያም አድርገን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስንልም በሥላሴ ማመናችንን እየመሰከርን ነው፡፡ በሥራችን መጨረሻም “ምስጋና ይሁን አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን” ብለን ሥራችንን በሥላሴ ስም ጀምረን በሥላሴ ስም እንፈጽማለን፡፡ሆኖም ግን ምስጢረ ሥላሴ ለሰው አእምሮ እጅግ የረቀቀ ስለሆነ የሰው አእምሮ ሊያውቅ የሚችለው እግዚአብሔር በገለጠለት መጠን ብቻ ነው፡፡

الفئة

عرض المزيد

تعليقات - 453